2025
“የዚህ ዓለምን ነገር በመተው” እንዴት ነው በዓለም ውስጥ የምንኖረው?
መጋቢት 2025 (እ.አ.አ)


ወርኃዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልእክት፣ መጋቢት 2025 (እ.አ.አ)

“የዚህ ዓለምን ነገር በመተው” እንዴት ነው በዓለም ውስጥ የምንኖረው?

ኢየሱስ ክርስቶስ የኔፋይት ደቀ መዛሙርትን ሾመ

የመረጣቸው ደቀ መዛሙርት፣ በኬሲ ቻይልድስ

ጌታ እንዳለው፣ “የዚህን አለም ነገሮች ወደጎን ትተያቸዋለሽ እናም የተሻሉ ነገሮችን ትሺያለሽ።” (ትምህርት እና ቃልኪዳን 25፡10)። ይህ ማለት ጊዜያዊና ቁሳዊ ፍላጎታችንን ችላ እንላለን ማለት አይደለም። ነገር ግን ልባችንን በሃብት፣ በስልጣን፣ ወይም በአለም ሞገስ ላይ አናስቀምጥም ማለት ነው። በዓለም መኖርን በተመለከተ የተማርናቸው አንዳንድ መርሆች የሚከተሉት ናቸው።

የእግዚአብሄርን ነገርመጃመሪያአስቀድሙ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። (ማቴዎስ 6፡33) በልባችን እና በህይወታችን ውስጥ፣ የእግዚአብሔር ትእዛዛት እና ከእርሱ ጋር ያለን ቃል ኪዳን ቅድሚያ የምንሰጣቸው ናቸውእኛን በአንድ ላይ የሚያስተሳስረን ለአዳኙ ያለን የግል እና የጋራ ፍቅር እንዲሁም ከእርሱ ጋር የገባነው ቃል ኪዳን ነው።

ለመማር ፈልጉ “ዙሪያችሁ ስላለው አለም ስትማሩ፣ ስለ አዳኝም ተማሩ… ብዙ ባወቅህ መጠን የአምላክን መንግሥት ለመገንባትና በዓለም ላይ በጎ ተጽዕኖ ለማሳደር ይበልጥ ጥረት ማድረግ እንችላለን” (ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ [2022]፣ 31፣ 32)

ስራ “ስራ አስፈላጊ የወንጌል መርህ ነው። እድገት እንዲኖር ከማድረጉም በላይ እድገት እንድናደርግ ያበረታታናል። … ጌታ ለቤተሰቦቻችን የሚያስፈልገውን እንድናቀርብ ብቻ ሳይሆን ‘በመልካም ነገር እንድንሳተፍ’ ይፈልጋል [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፡27]” (“ሥራ፣” ርዕሰ ጉዳዮች እና ጥያቄዎች፣ የወንጌል ቤተ መጻሕፍት)።