“የሮሊንስ እህታማቾች ቀኑን አዳኑት!” ጓደኛ፣ ሰኔ 2021 (እ.አ.አ)
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ ሰኔ 2021 (እ.አ.አ)
የሮሊንስ እህታማቾች ቀኑን አዳኑት!
ሥዕል በአፕርይል ስቶት
ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን የሚረዱንን በርካታ ጠቃሚ ነገሮቸ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ነገረው። ቤተክርስቲያኗ የኢየሱስ ክርስቶስን ቃላት ለማተም ማተሚያ ቤት አቋቋመች። በዚያውም መንገድ ሰዎች እነዚህን ሊያነቧቸው ይችላሉ።
አንድ ቀን የተናደዱ ሰዎች መጡ። ማተሚያ ቤቱን አፈረሱት። የቅዱሳን ጽሁፎቹን ገጾቸ በየመንገዱ ላይ ወረወሩ።
ሜሪ ኤልሳቤት እና ካሮሊን ሮሊንስ እየተካሄደ የነበረውን ተመለከቱ። ሮጠው ገጾቹን በእቅፎቻቸው ሰበሰቡ።
ልጃገረዶቹ ሰዎቹ እስኪሄዱ ድረስ በበቆሎ ማሳ ውስጥ ተሸሸጉ። ቅዱሳን ጽሁፎቹን አትርፈዋቸው ነበር! እነዚያ ቅዱሳን ጽሁፎች በኋላ ላይ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል ሆኑ።
ቅዱሳን ጽሁፎችን ማንበብ እችላለሁ። ደፋር እና ላመንኩበት ነገር የምቆም መሆን እችላለሁ።
የሚቀባ ገፅ
ደፋር መሆን እችላለሁ
ደፋር እንድትሆኑ ምን ሊረዳችሁ ይችላል?
© 2021 በIntellectual Reserve, Inc. መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, June 2021 ትርጉም። Amharic. 17470 506