“ለ2021 (እ.አ.አ) ስርዓተ-ትምህርት መመሪያዎች፣” ለ2021 (እ.አ.አ) ስርዓተ-ትምህርት መመሪያዎች [2020 (እ.አ.አ)]
“ለ2021 (እ.አ.አ) ስርዓተ-ትምህርት መመሪያዎች፣” ለ2021 (እ.አ.አ) ስርዓተ-ትምህርት መመሪያዎች
ለ2021 (እ.አ.አ) ስርዓተ-ትምህርት መመሪያዎች
ይህ ሰነድ በ2021 (እ.አ.አ) ጥቅም ላይ የሚውሉ የቤተክርስትያን ስርዓተ-ትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ይዘረዝራል። ለአብዛኛዎቹ ቋንቋዎች እነዚህ የጥናት ምንጮች በወንጌል ቤተ-መጽሐፍት መተግበሪያ አፕልኬሽን ውስጥ እና በComeFollowMe.ChurchofJesusChrist.org ላይ ይገኛሉ። ለ2021 (እ.አ.አ) የሚሆኑ አዲስ መረጃዎች በዚህ ተጠቅሰዋል።
ግለሰቦች እና ቤተሰቦች
አዲስ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) (16587)
የቤተክርስቲያን ክፍላችሁ አባላት ሂሊጋይነን፣ ሲንሃላ፣ ቱርክኛ፣ ህንድኛ፣ ታሚል፣ ተሉጉ ወይም ኡርዱ ተናጋሪ ከሆኑ፣ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) (16899)ን ተጠቀሙ።
የመጀመሪያ ክፍል
የህጻናት ክፍል (ከ18 ወር–2 አመት)
ህፃናቶቻችሁን ተመልከቱ፥ የህጻናት ክፍል የትምህርት መምሪያ (37108)
የመዝሙር ጊዜ እና ሁሉም የመጀመሪያ ክፍሎች (ከ 3-11 አመት)
አዲስ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) (16588)
የቤተክርስቲያን ክፍላችሁ አባላት አማርኛ፣ ሂሊጋይነን፣ ህንድኛ፣ ህሞንግ፣ አይስላንድኛ፣ ላኦ፣ ሊንጋላ፣ ሰርብያኛ፣ ሾና፣ ሲንሃላ፣ ስሎቫክኛ፣ ስሎቬንኛ፣ታሚል፣ ተሉጉ፣ ቱርክኛ፣ ኡርዱ፣ ቆኦሳ፣ ወይም ዙሉ ተናጋሪ ከሆኑ፣ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)ን ለመጀመሪያ ክፍል ተጠቀሙ፣ ወይም ሌሎች የቤተክርስትያን መመርያዎችን ተጠቀሙ።
የሰንበት ትምህርት ቤት
የአዋቂዎች እና የወጣቶች የሰንበት ትምህርት ቤት
አዲስ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለሰንበት ትምህርት ቤት፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) (16589)
የክፍላችሁ አባላት አማርኛ፣ ሂሊጋይነን፣ ህንድኛ፣ ህሞንግ፣ አይስላንድኛ፣ ላኦ፣ ሊንጋላ፣ ሰርብያኛ፣ ሾና፣ ሲንሃላ፣ ስሎቫክኛ፣ ስሎቬንኛ፣ ታሚል፣ ተሉጉ፣ ቱርክኛ፣ ኡርዱ፣ ቆኦሳ ወይም ዙሉ ተናጋሪ ከሆኑ፣ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፡ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)ን ለሰንበት ትምህርት ተጠቀሙ፣ ወይም ከሌሎች የቤተክርስትያን መመርያዎች ተጠቀሙ።
የሽማግሌዎች ሸንጎ እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር
“ከአጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶች መማር“ (በኢንዛይን ወይም ሊያሆና ጉባኤ እትም ውስጥ ይገኛል።)
የቤተክርስቲያን ክፍላችሁ አባላት አማርኛ፣ ሂሊጋይነን፣ ህንድኛ፣ ህሞንግ፣ አይስላንድኛ፣ ላኦ፣ ሊንጋላ፣ ሰርብያኛ፣ ሾና፣ ሲንሃላ፣ ስሎቫክኛ፣ ስሎቬንኛ፣ ታሚል፣ ተሉጉ፣ ቱርክኛ፣ ኡርዱ፣ ቆኦሳ፣ ወይም ዙሉ ተናጋሪ ከሆኑ፣ የሽማግሌዎች ሸንጎ ወይም የሴቶች መረዳጃ አባላትን ፍላጎት ለማሟላት ከሚችል ከቅርብ ጊዜ አጠቃላይ ጉባኤ መልእክት አስተምሩ፣ ወይም ሌሎች የቤተክርስትያን መመሪያዎችን ተጠቀሙ።
አሮናዊ ክህነት እና ወጣት ሴቶች
አዲስ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለአሮናዊ ክህነት ሸንጎዎች እና ለወጣት ሴቶች ክፍሎች፥ ትምህርታዊ ርዕሶች 2021 (እ.አ.አ) (16639)
የክፍላችሁ አባላት አማርኛ፣ ሂሊጋይነን፣ ህንድኛ፣ ህሞንግ፣ አይስላንድኛ፣ ላኦ፣ ሊንጋላ፣ ሰርብያኛ፣ ሾና፣ ሲንሃላ፣ ስሎቫክኛ፣ ስሎቬንኛ፣ ታሚል፣ ተሉጉ፣ ቱርክኛ፣ ኡርዱ፣ ቆኦሳ፣ ወይም ዙሉ ተናጋሪ ከሆኑ፣ በወንጌሌን ስበኩ (16229) ምዕራፍ 3 ውስጥ ያሉትን ትምህርቶች ተጠቀሙ። ደግሞም የወጣቶቻችሁን ፍላጎት ለማሟላት ከሚችል ከቅርብ ጊዜ አጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶች ማስተማርም ትችላላችሁ።
ሁሉም ድርጅቶች
የአስተማሪ ሸንጎ ስብሰባ
በአዳኙ መንገድ ማስተማር
ሌሎች ትምህርቶች (ሌሎች መመሪያዎች የሚገኙ ከሆኑ)
ትዳርን እና ቤተሰብን ማጠናከርያ፣ የቤተመቅደስ ዝግጅት፣ እና የሚስዮናዊነት ዝግጅት ትምህርቶች በሁለተኛው የቤተክርስትያን ሰአት አይካሄዱም። ሆኖም፣ በኤጲስ ቆጶስ ውሳኔ እና በክልል ጉዳይ አስፈላጊነቱ፣ እነዚህ ትምህርቶች በሌሎች ጊዜዎች ለግለሰብ፣ ለቤተሰብ እና ለቡድኖች ሊሰጡ ይችላሉ።
ትዳር እና የቤተሰብ ግንኙነቶች
ትዳር እና የቤተሰብ ግንኙነቶች ትምህርቶች የአስተማሪ መመሪያ (35865) እና ትዳር እና የቤተሰብ ግንኙነቶች የተሳታፊዎች የጥናት መመሪያ (36357)
የቤተ-መቅደስ ዝግጅት
Endowed from on High: Temple Preparation Seminar Teacher’s Manual (36854) and Preparing to Enter the Holy Temple (36793)
ለቤተክርስቲያን ክፍል አመታዊ ስርዓተ-ትምህርትን ለማዘዝ የሚጠቅሙ መመሪያዎች
ለ2021 (እ.አ.አ)፣ ኤጲስ ቆጶሳት እና የቅርንጫፍ ፕሬዘዳንቶች የታተሙ የኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች ግልባጮችን በቤተክርስቲያን ክፍላቸው ውስጥ ለማሰራጨት ይቀበላሉ። በቤተክርስቲያን ክፍል ውስጥ ላሉ ለእያንዳንዱ ተሳታፊ ቤተሰብ አንድ ቅጂ ይሰጣል። የአካባቢው የቤተክርስቲያን ክፍሎችም ለእነዚህ ቅጂዎች እንዲከፍሉ አይጠየቁም። ሆኖም፣ የቤተክርስቲያን ክፍሎች በመጀመሪያ ክፍል፣ በሰንበት ትምህርት ቤት፣ በአሮናዊ ክህነት እና በወጣት ሴቶች ጥቅም ላይ የሚውሉ የታተሙ መመሪያ ቅጂዎችን ለማግኘት ማዘዝ እና መክፈል ያስፈልጋቸዋል።
እነዚህን የቤተክርስቲያን ክፍል የትምህርት መመሪያዎችን ከሰኔ 30 2020 (እ.አ.አ) ጀምሮ ማዘዝ ይችላሉ። እባካችሁ ትዕዛዛችሁን ከነሐሴ 31 2020 (እ.አ.አ) በፊት ላኩ። ከዚህ ቀን በኋላ የሚታዘዙ የትምህርት መመሪያ ትዕዛዞቸ በጥር 1 ቀን 2021 (እ.አ.አ.) ላይ ሊደርሱ የማይችሉ ይሆናሉ፡፡ የታተሙ ቅጂዎችን ለማዘዝ store.ChurchofJesusChrist.org ይጎብኙ፣ Units and Callings [ክፍሎች እና ጥሪዎች]ን ይምረጡ፣ እና ከዚያም Annual Curriculum [አመታዊ ስርአተ ትምህርት]ን ይምረጡ።
ከሚያስፈልጋችሁ በላይ ቅጂዎችን እንዳታዙ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ግምት ውስጥ አስገቡ፥
-
ቀድሞውኑ የቤተክርስቲያን ክፍላችሁ ከእያንዳንዱ ርእስ ምን ያህል የታተሙ ቅጂዎች አሉት?
-
ምን ያህል አስተማሪዎች ከታተመ ቅጂ ይልቅ ዲጂታል መሳርያዎችን ይጠቀማሉ?
የአካል ጉዳት ላላቸው መገልገያዎች
በድምጽ፣ በብሬል እና በትልቅ ፊደላት የታተሙ መገልገያዎች በstore.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ ይገኛሉ።