2010–2019 (እ.አ.አ)
ዘለአለማዊ ውሳኔ
ኦክተውበር 2013


14:26

ዘላለማዊ ውሳኔ

ጥበባዊ የሆነ ሰው ነፃነቱን ተጠቅሞ ለአሁን እና ዘላለማዊ ውሳኔ ማድረግ ለመንፈሳዊ ዕድገቱ አስፈላጊ ነው።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች እያንዳንዱ ቀን የውሳኔ ቀን ነው። ፕሬዝዳንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን ውሳኔ አስቀድሞ የመወሰን እጣ ፋንታ እንደሆነ አስተምሮናል። ጥበባዊ የሆነ ሰው ነፃነቱን ተጠቅሞ ለአሁን እና ዘላለማዊ ውሳኔ ማድረግ ለመንፈሳዊ ዕድገቱ አስፈላጊ ነው። ለመማር በፍፁም ልጆች አይደላችሁም ለመለወጥም ያረጀ አይደላችሁም። ለመማር እና ለመለወጥ ፍላጎታችሁ የሚመጣው ከመለኮታዊ ዕድገት መጣጣር ነው። እያንዳንዱ ቀን ለዘላለማዊ ውሳኔ ዕድል ያመጣል።

እኛ የሰማይ ወላጆች መንፈሳዊ ልጆች ዘላለማዊ ፍጡሮች ነን። መፅሀፍ ቅዱስ እንደጠቀሰው፣ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። በቅርቡ ተወዳጅ የሆነው የልጆች መዝሙር እኔ የእግዚአብሄር ልጅ ነኝ የሚለውን ሰምቼ ነበር። ተገርምኩኝ፣ በእናቶች እና ታምኝ አባቶች አልፎ አልፎ ይህን ስዘምሩ ለምን አልሰማሁም? ሁላችንም የእግዚአብሄር ልጆች አይደለንም? ስለ እውነት ማናችንም የእግዚአብሄር ልጆች አለመሆናችን በፍፁም ማቆም አንችልም

እንደ እግዛብሄር ልጅነታችን በሙሉ ልባችን እና ነፍሳችን እሱን ከምድራዊ ቤተሰባችን የበለጠ መወደድ አለብን።. ጎሮበታችን እንደ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን መውደድ አለብን። ከዝህ የበለጠ ትዕዛዝ የለም። የሰዎች ህይወት ዋጋን በብዙ ደረጃ በፍፁም መወደስ የለብንም።

የሰው አካልና መንፈስ የሰዎች ህይወት እንደሆነ ቅዱስ መፅሀፍ ታስተምራል።. እንደ ጥንድ ፍጡር እያንዳንዳችሁ ዋጋ ልገመት ለማይችለው የአካልና መንፈስ ስጦታ እግዚአብሄርን ማመስገን አለባችሁ።

የሰው አካል

ለብዙ አመታት የህክምና ዶክተርነት ሙያዬ ለሰው ልጆች አካል ታላቅ ክብር እንድሰጥ አድርጎኛል። ለናንቴ እንደ ስጦታ በግዚአብሄር የተፈጠረ ነው፣ በፍፁም የሚያስገርም ነው። የሚያይ አይናችሁ፣ የሚሰማ ጆሮአችሁ እና የሚዳሥስ ጣታችሁን አስቡ። አንጎላችኈንድትማሩ፣ እንድታስቡ ያደርጋል። ልባችሁ እናንተ ሳታውቁ ያለድካም ቀንና ሌሊት ይነፋል።

ሰውነታችሁ እራሱን ይጠብቃል። ህመም እንደ ማስጠንቀቂያ አንድ ነገር ትክክል እንዳልሆነ እና ትኩረት እንድደረግ ተብሎ ይመጣል። የቁስል ህመም ከጊዜ ወደ ጊዜ ይመጣል፣ ፀረ እንግዳ አካል በመፈጠር ቅስሉን እንድከላከል ያደርጋል።

አካላችሁ እራሱ ይጠግናል። ቁስል እና ሠንበር ይድናል። የተሰበረ አጥንት እንደገና ጠንካራ ይሆናል። እግዚአብሄር ከሰጣችሁ ብዙ ጥረት ያለው አካላችሁ ጥቅቶቹን ጠቅሻለሁ።

ምንም እንኳ በእያንዳንዱ ሰው ባይሆንም በአንዳንድ ቤተሰቦች ልዩ እንክብካቤ የሚስፈልጋቸው የአካል ሁነታዎች ይኖራሉ። ይህን ፈተና ለመቋቋም በጌታ የተሰጠ ዛዴዎች አሉ። ሰዎች ትሁት እንዲሆኑ ድካምን እሰጣቸዋለሁ፤ እናም ፀጋዬም እራሳቸውን በፊቴ ዝቅ ላደረጉ ሁሉ በቂ ነው፤ እነርሱም በፊቴ እራሳቸውን ዝቅ ካደረጉ እናም በእኔም እምነት ካላቸው ደካማ የሆኑትን ጠንካራ እንዲሆኑ አደርጋለሁ።

አንዳኔ የኮከብ መንፈስ ፍፁም ባልሆነ አካል ልኖር ይችላል። የዝህ አይነት አካል ስጦታ ወላጆችን እና ልጆች ልዩ እንክብካቤ ለሚያስፍልገው የተወለደ ልጅ ጋር ህይወታችዋ እንድያዳብሩ ይረዳቸዋል።

የማርጀት ስጦታ ሂደት የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፣ ሞትም ስጦታ ነው። የሟችነት አካላችሁ ለእግዚአብሄር ታላቅ ዕቅድ ደስታ አስፈላጊ ነው። ለምን? ምክንያቱም ሞት መንፈሳችሁ ወደ እሱ እንድመለስ ያደርጋል። ከዘላለማዊ ገፅታ አመለካከት ሞት ያል ጊዜው የተከሰተ የሚሆነው ከእግዚአብሄርን ጋር ለመገናኘት ላልተዘጋጁ ብቻ ነው።

አካላችሁ ለእግዚአብሄር ዘላለማዊ ዕቅድ ዋነኛ አካል መሆን፣ ሀዋሪያው ጳውሎስ የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ ማለቱ የምያስገርም አይደለም። መስታወት ስትመለከቱ አካላችሁ በተመቅደሳችሁ መሆኑን ተመልከቱ። እውነታው በየቀኑ ለአካላችሁ እንደት እንደምታስቡ እንደት እንደምትጠቀሙ ውሳኔያችሁ ላይ ትፅዕኖ ያደርጋል። ይህም ውሳኔ የእጣ ፋንታችሁን ያረጋግጣል። ይህ እንዴት ልሆን ይችላል? ምክንያቱም አካላችሁ ለመንፈስ ቤተመቅደስ ነው። አካላችሁን እንዴት እንድምትጠቀሙ መንፈስ ላይ ውጤት ያመጣል። ዘላለማዊ ጉዞያችሁን የሚወስኑ አንዳንድ ውሳኔዎች ያቀፉት፣

  • አካልችሁን እንዴት መንከባከብ እና መጠቀም አለባችሁ?

  • የትኛውን መንፈሳዊ ባህርይ ለማዳበር ትመርጣላችሁ?

የሰዎች መንፈስ

መንፈሳችሁ ለዘላለም ብቻውን መኖር ይችላል። ጌታ ለነቢዩ አብረሀም ከመወለድህ በፍት ተመርጠሀል አለው። ጌታ እንድዚሁ ተመሳሳይ ለኤርምያስና ሌሎች ብዙዎች ብሏል። ስለ እናንተ እንኳ ተናግረዋል።

የሰማይ አባታችሁ ለብዙ ጊዜ አውቆአችዋል። በዝህን ወቅት እንደ ወንድ ልጁና ሴት ልጅ ወደ ምድር መጥታችሁ ለምድር ላይ ታላቅ ሥራው መሪዎች እንድትሆኑ መረጣችሁ። የተመረጣችሁ ለአካልችሁ ባህርይ ሳይሆንለመንፈስ ባህሪያችሁ ነው። ይህም በጀግንነት፣ በጉብዝና፣በልበ ንፁህ ታማኝነት፣ ለእውነት ጥማት፣ ለጥበብ በመራብ እና ሌሎችን ለማገልገል ፍላጎትን ያመጣል።

እንኝህን ባህሪይዎች ከመወለዳችሁ በፍት አዳብራችዋል። ሌሎች በዚህች ምድር ላይ በመፈለግ ማዳበር ትችላላችሁ።

ዋናው የመንፈሳዊ ባህርይ እራስን መቆጣጠር ነው፣ የመብላት ፍላጎት ላይ ምክንያት ለማድረግ ብርታትን ማግኘት ነው። እራስን መቆጣጠር ጠንካራ ህሊና ያዳብራል። ህሊናችሁ አስቸጋሪ ነገር እና ፈተና ስያጋጥማችሁ ለስነምግባር አመላለሳችሁን ይወስናል። ፆም ማድረግ መንፈሳችሁን በማዳበር የመብላት ፍላጎትን እንድቋቋም ይረዳል። ፆምና ፀሎት የሰማይ እርዳታን ይጨምርላችዋል። እራስን መቆጣጠር ለምን አስፈለገ? እግዚአብሄር ለሰው ዘሮችዋነኛ የሆነውን የማፍቀር እና የመመገብ ፍላጎት ተክሎብናል። በእግዚአብሄር ህግ ራሳችን ስንገዛ በረጅም ህይወትና ታላቅ ፍቅር መደሰት እንችላለን።

ስለዝህ የሚያስገርም አይደለም፣ ከእግዚአብሄር የእቅድ ደስታ የመባከን ፈተና የሚመጣው አስፈላጊ የሆነውን እግዚአብሄር የሰጣን ፍላጎት ካለ አግባብ ስንጠቀም ነው። ፍላጎታችን መቆጣጠር ሁል ጊዜ ቀላል አይደለም። ማናችንም ፍፁም በሆነ መቆጣጠር አንችልም። ስህተት ይፈጠራል፣ መሳሳት ይደረጋል። ሀጢያት ይደረጋል። ስለዝህ ምን ማድረግ አለብን? ክዝሁ መማር እንችላለን። እናም እውነተኛ የሆነ ንሰሀ መግባት እንችላለን።

ባህርያችን መቀየር እንችላለን። ፍላጎታችን ልቀየር ይችላል። እንዴት? አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው። እውነተኛ እና ቋሚ ለውጥ ልመጣ የሚችለው በምያድነው እና በሚያነፃው የኢየሱስ ክርስቶስ ሀጢያት ክፍያ ሀይልብቻ ነው። እሱ እያንዳንዳችሁን ይወዳል። ትዕዛዙን በፍላጎት እና ከልብ በትክክል የሚትጠብቁ ከሆነ የእርሱን ሀይል እንድታገኙ ያደርጋችዋል። ቀላልና እርግጠኛ የሆነ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልis የለውጥ ወንጌል ነው።

ሥጋዊ አካልን የሚቆጣጠር ሀይለኛ የሰው ዘር መንፈስ በጥልቅ ስሜት ሥር ባሪያ ሳይሆን አዛዥ ነው። የዝህ አይነት ነፃነት ኦክስጅን ለአካል አስፈላጊ እንደሆነ ይህም ለነፍስ በጣም አስፈላጊ ነው።ከራስ ባሪነት መላቀቅ እውነተኛ ነፃነት ነው።

እኛ ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ ነፃ ነን፣ ወይም እስረንነትን፣ ስቃይን እና ሞትን ለመምረጥ ነፃ ነን። ወደ ዘላለማዊ ህይወትና የነፃነት መንገድ ግብረገብነት አስተሳሰብ ስንመርጥ ያ መንገድ ጋብቻን ያቀፈ ይሆናል። የኃለኛው ቀን ቅዱሳኖች በወንድና በሴት መሀከል ያለው ጋብቻ በግዚአብሄር የታወጀ መሆኑን ያውቃሉ። እናም ለፈጣሪ ልጆች ዘላለማዊ ዕቅድ ጉዞ ቤተሰቦች ዋነኛ አስፈላጊ እንደሆኑ ናቸው። ፆታም ከመወለዳቸው በፍት እና በምድር እናም ለዘላለማዊ አላማ አስፈላጊ የሆነ መለያ ባህሪይ መሆኑን እናውቃለን።

በወንድና በሴት መካከል ያለው ጋብቻ ለጌታ ህግጋት እና ለእግዚአብሄር ዘላለማዊ እቅድ መሰረታዊ ነው። በወንድና በሴት መካከል ያለው ጋብቻ በምድር እና ስማይ ሙሉ ህይወት የሚሰጥ የእግዝአብሄር ንድፍ ነው። የእግዚአብሄር ጋብቻ ንድፍን መስደብ፣አለመግባባት ወይም አዛብቶ መተርጎም አይቻልም። እውነተኛ ደስታ የሚትፈልጉ ከሆነ! የእግዚአብሄር ጋብቻ ንድፍ ቅዱስ የሆነ ነፍስ የመፍጠር ሀይልን እና የጠበቀ የጋብቻ ወዳጅነትን ደስታን ይጠብቃል። አዳምና ህዋን የባልና ምስትነት ደስታ ልምድ ከማግኘታቸው በፍት በግዚአብሄር እንደተጋቡ እናውቃለን።

በዘመናችን መንግስት ጋብቻን ለመጠበቅ ፍላጎት አላቸው፣ ምክንያቱም ጠንካራ ቤተሰብ ለጤንነት፣ ለትምህርት፣ ለበጎአድራጊነት እና በማደግ ላይ ላሉት ትውልዶች ብልፅግና ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለምያደርጉ ነው። ነገር ግን መንግስት በማህበራዊ ዝንባሌ እና መንፈሳዊ ባልሆኑ ፈላስፋዎች ተፅእኖ አድሮባቸዋል። እነሱም ህግን ለማስጠበቅ ደጋግመው ይፅፋሉ። ምንም እንኳ ህግ አውጪዎች የፈለጉትን ብያሳልፉ ስለጋብቻ እና ቅድስና የጌታ ህግጋት ሊለወጥ አይችልም። ምንም እንኳ ሀጥያት በህግ አውጭዎች ብወጣም በእግዚአብሄ ፍት ሀጢያት መሆኑን አስታውሱ።

የአዳኝን ርህራሄ የበለጠ በማሰብ ለግዚአብሄር ልጆች መብትና ስሜት ዋጋ ብንሰጥም ህግጋቱን መቀየር አንችልም። ለመለወጥ የኛ መብት አይደለም። የእሱ ህግጋት ማጥናት፣ መረዳት እና መደገፍ አንብን።

የአዳኝ የህይወት መንገድ ጥሩ ነው። መንገዱም ከጋብቻ በፍት ንፅህናን ያቀፈ እና ከጋብቻ በኃላም ሙሉ ታማኝነት ያስፈልጋል። ዘላቂ የሆነ የደስታ ልምድ የሚናገኘው በጌታ መንገድ ብቻ ነው። የእሱ መንገድ ለነፍሳችን ቋሚ ፅናት እና ለቤታችን ስላምን ያመጣል። እናም ከሁሉም በላይ የእርሱ መንገድ ወደ እሱ ቤት እና የሰማይ አባታችን ዘላለማዊ ህይወት ይመራናል። ይህ የእግዚአብሄር ሥራና ክብር ነው።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች እያንዳዱ ቀን የውሳኔ ቀን ነው። እና ውሳኔያችን ጉዞያችን ይወስናል። አንድ ቀን ሁላችንም ለዳኝነት በጌታ ፍት እንቆማለን። ሁላችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የግል ቃለ መጠይቅ ይኖረናል። ስለ አካላችን፣ስለ መንፈሳዊ ባህሪያችን እና ስለ እግዚአብሄር ጋብቻ ንድፍ እንዴት ክብር እንደሰጠን እና ስለ በቤተስ ያደረግነው ውሳኔያችን ተጠያቂዎች ነን። ይህንን ዘላለማዊ ውሳኔ በየዕለቱ ጥበባዊ በሆነ መምረጥ እንዳለብን የልብ ፅሎቴ በተቀደሰው ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. Thomas S. Monson, “Decisions Determine Destiny” (Church Educational System fireside, Nov. 6, 2005), 3; speeches.byu.edu

  2. የዘለአለማዊ እድገት ሀሳብ በደብሊው. ደብሊው. ፌልፕስ በመዝሙር ቁጥር 284 ቃላት “If You Could Hie to Kolob” (Hymns, በደንብ ተመዝግቦ ነበር። አራተኛው አንቀጽ እንዲህ ይነበባል፥ “ለምግባር ምንም መጨረሻ የለም/ ለሀይል ምንም መጨረሻ የለም፤/ ለጥበብ ምንም መጨረሻ የለም፤/ ለብርሀን ምንም መጨረሻ የለም።/ ለአንድነት ምንም መጨረሻ የለም፤/ ለወጣትነት ምንም መጨረሻ የለም፤/ ለክህነት ምንም መጨረሻ የለም፤/ ለወጣትነት ምንም መጨረሻ የለም።” አንቀጽ 5ም እንዲህ ይላል፥ “ለክብርምንም መጨረሻ የለም፤/ ለፍቅር ምንም መጨረሻ የለም፤/ ለህይወት ምንም መጨረሻ የለም፤/ በላይም ሞት የለም።”

  3. ዘፍጥረት 1:27፤ ደግሞም ቄላስይስ 3:10 ተመልከቱ፤ አልማ 18:34ኤተር 3:15ሙሴ 6:9

  4. “I Am a Child of God,” Hymns, no። 301።

  5. ማቴዎስ 10:37 ተመልከቱ

  6. ማርቆስ 12:30–31 ተመልከቱ።

  7. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 88:15

  8. በሰውነታችሁ በእግዚአብሔር የተሰጡ ሌሎች ነገሮችም አሉ። ሶዲየም፣ ፖታሲየም፣ ካልሲየም፣ እና ውሀ፣ ግሉኮስ፣ እና ፕሮቲን ለህይወት አስፈላጊ ናቸው። ሰውነትም ኦክስጂን እና ካርቦን ዳኢ ኦክሳይድ አየሮችንም ይጠቀማል። ኢንሱሊን፣ አድረንሊን፣ እና ታይሮክሲን ሆርሞንንም ይጠቀማል። የእነዚህ ነገሮች መጠን እና ሌሎች ነገሮች በሰውነት ውስጥ በቁጥጥር በጥቅም ላይ ይውላሉ። እነዚህ ሆርሞኖች የሰውነት ስራን በመቆጣጠር የሰውነታችሁ ሙቀትን በ 98.6˚F or 37˚C ያስተካክላሉ።።

  9. Some conditions are easily evident; others are latent። Some are familial; others are not። Some people are predisposed to cancer, others have allergies, and so on። Each of us can be alert to his or her own area of weakness and humbly learn what the Lord would teach, that the weakness may become a strength።

  10. ኤተር 12:27

  11. Some conditions won’t be fully corrected until the Resurrection, when “all things shall be restored to their proper and perfect frame” (አልማ 40:23)።

  12. አልማ 42:8

  13. The Psalmist wrote, “Precious in the sight of the Lord is the death of his saints” (መዝሙር 116:15)። Death is precious because it is a “homecoming” for the Saint with the Lord።

  14. 1 ቆሮንጦስ 3:16፤ ደግሞም 6:19 ተመልከቱ።

  15. አብርሐም 3:23

  16. ኤርምያስ 1:5

  17. አልማ 13:2–3

  18. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 138:55–56

  19. አልማ 13:2–3; ትምህርት እና ቃል ኪዳን138:38–57

  20. Attributes of “faith, virtue, knowledge, temperance, patience, brotherly kindness, godliness, charity, humility, [and] diligence” (ትምህርት እና ቃል ኪዳን 4:6) are among the spiritual gifts we can develop and be given። Gratitude is another spiritual attribute that can be developed. Gratitude shapes mood and productivity። And when you have “spiritually been born of God,” you may gratefully receive His image in your countenance (see አልማ 5:14)።

  21. 1 ቆሮንጦስ 1214:1–12ሞሮኒ 10:8–19; ትምህር እና ቃል ኪዳን 46:10–29

  22. Some are tempted to eat too much። “Obesity has reached epidemic proportions globally, with at least 2.8 million people dying each year as a result of being overweight” (“10 Facts on Obesity,” World Health Organization, Mar. 2013, www.who.int/features/factfiles/obesity/en). Others are tempted to eat too little። Anorexia and bulimia devastate many lives, marriages, and families። And some are tempted by sexual appetites forbidden by our Creator። Clarification is found in Handbook 2: Administering the Church, which states: “The Lord’s law of chastity is abstinence from sexual relations outside of lawful marriage and fidelity within marriage። … Adultery, fornication, homosexual or lesbian relations, and every other unholy, unnatural, or impure practice are sinful።” Still quoting from the handbook: “Homosexual behavior violates the commandments of God, is contrary to the purposes of human sexuality, and deprives people of the blessings that can be found in family life and in the saving ordinances of the gospel። … While opposing homosexual behavior, the Church reaches out with understanding and respect to individuals who are attracted to those of the same gender” ([2010], 21.4.5; 21.4.6)።

  23. 1 ቆሮንጦስ 6:9–20ያዕቆብ 1:25–27ትምህርት እና ቃል ኪዳን 130:20–21። ሰዎች ደስታ እንዲኖራቸው እንደተፈጠሩ ሁልጊዜም ማስታወስ አለብን (2 ኔፊ 2:25)።

  24. Mortality is a period of testing, as explained in scripture: “We will prove them herewith, to see if they will do all things whatsoever the Lord their God shall command them” (አብርሐም 3:25)።

  25. ሞዛያ 4:10አልማ 39:9ሔላማን 15:7Handbook 2 includes this message: “Homosexual behavior can be forgiven through sincere repentance” (21.4.6)።

  26. Through the Atonement of Jesus Christ and by obedience to the principles of the gospel, all mankind may be saved (see ትምህርት እና ቃል ኪዳን 138:4የእምነት አንቀጽ 1:3)።

  27. ኤተር 12:33–34ሞሮኒ 8:17

  28. ሞዛያ 5:2አልማ 5:12–14

  29. ሮሜ 8:13–17ገላትያ 5:13–25ትምህርት እና ቃል ኪዳን 88:86

  30. 2 ኔፊ 2:27

  31. See ትምህርት እና ቃል ኪዳን 131:1–4

  32. “The Family: A Proclamation to the World,” Ensign or Liahona, Nov. 2010, 129።

  33. See ማቴዎስ 19:4–6ሞዛያ 29:26–27ሔላማን 5:2

  34. Each person is born with unique identity, chromosomes, and DNA (deoxyribonucleic acid)። DNA is a molecule that encodes genetic instructions used in the development and function of living cells። Each person’s DNA is created when the DNA from a father and a mother combine to create the DNA of a new body—a partnership between father, mother, and child።

  35. See ዘፍጥረት 2:24–253:20–214:1–2, 25

  36. Dr. Patrick F. Fagan wrote: “The indispensable building block upon which the fortunes of the economy depends [is] the married-parent household—especially the child-rich family that worships weekly። … Every marriage creates a new household, an independent economic unit that generates income, spends, saves, and invests” (“The Family GDP: How Marriage and Fertility Drive the Economy,” The Family in America, vol. 24, no. 2 [Spring 2010], 136)።

  37. ዘጸአት 20:14ዘሌዋውያን 18:2220:13ዘኁልቁ 5:18ማቴዎስ 5:27–28ማርቆስ 10:19ሉቃስ 18:20ሮሜ 1:26–2713:9ሞዛያ 13:223 ኔፊ 12:27–28ትምህርት እና ቃል ኪዳን 42:2459:6

  38. Gordon B. Hinckley, “This Thing Was Not Done in a Corner,” Ensign, Nov. 1996, 49 ተመልከቱ።

  39. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 14:7

  40. ሙሴ 1:39

  41. 2 ኔፊ 9:41, 46ሞዛያ 16:10

  42. We will be judged according to our deeds and the desire of our hearts (see ትምህርት እና ቃል ኪዳን 137:9ዕብራውያን 4:12አልማ 18:32ትምህርት እና ቃል ኪዳን 6:1688:109)።