ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ጥቅምት 2025 (እ.አ.አ)
ጌታ ለምን ቤተክርስቲያን አለው?
የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አላማ "ግለሰቦች እና ቤተሰቦች እግዚአብሔር የማዳን እና ከፍ ከፍ የማድረግ ስራውን እንዲፈጽም እንዲረዱት ለማስቻል" ነው። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን “[የእግዚአብሔርን] ልጆች ለከፍተኛው የክብር ደረጃ፣ ይህም ከፍ ከፍ ማድረግ ወይም የዘላለም ህይወት ለማግኘት ብቁ እንዲሆኑ” ይረዳል።
“አዳኙ… [ቤተክርስቲያንን] ያደራጀው በመስበክ፣ ስነስርዓቶቹን እና ቃል ኪዳኖቹን በማቅረብ እንዲሁም ኃይሉ እኛን ለማጽደቅ እናም ለመቀደስ እንዲያስችል በማድረግ የወንጌሉን ዓላማውን እንድትፈጽም።
የቤተክርስቲያኗ አባላት በክህነት ስልጣን እና ቁልፎች፣ ቃል ኪዳኖች እንዲሁም ስርዓቶች፣ ትንቢታዊ መመሪያ፣ ቅዱሳት መጻህፍት እና በቅዱሳን ማህበረሰብ በኩል የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይል እና በረከቶች ማግኘት ይችላሉ።
ቤተክርስቲያንም እንዲሁ ታዛለች፡- “ለሁላችሁም እውነት እላችኋለሁ፥ ለህዝቦች መመሪያ ትሆኑ ዘንድ ተነሱ እና አብሩ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥5)።
የቤተክርስቲያኗ አባላት በወንጌሉ በመኖር፣ ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ በመጋበዝ፣ ቤተሰቦችን በዘለአለም አንድ በማድረግ፣ እንዲሁም ድሆች እና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን በመንከባከብ "ብሩህ" ለመሆን ይጥራሉ። ይህ የእግዚአብሔር የማዳን እና ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ ነው።
© 2025 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly For the Strength of Youth Message, October 2025 ትርጉም። Amharic። 19624 506