2025
ኢየሱስ ክርስቶስ ለመልካም ቀናትም ጭምር ነው
ለወጣቶች ጥንካሬ መስከረም 2025 (እ.አ.አ)


ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ መስከረም 2025 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ክርስቶስ ለመልካም ቀናትም ጭምር ነው

ነገሮች በመልካም በሚሆኑበትን ጊዜያት እንኳን፣ በጌታ ላይ እንዴት ማተኮር እንችላለን? የሚከተሉት ጥቂት ሀሳቦች ናቸው።

የፈገግታ ፊት ከጸሃይ ተነጥሎ

ጓደኛችሁ በትግል ላይ በሆነበት ጌዜ ብቻ አብሯችሁ ሲሆን እና ደስተኛ በሆነበት ጊዜ ብቻ ከእናንተ ሲርቅ አስቡ። ጤናማ ግንኙነት ነውን? በእውነት አይደለም።

ለአዳኛችን ያንን እናደርጋለንን—እርሱን በአስቸጋሪ ጊዜያት እንፈልገዋለን እና በመልካም ቀናት እንረሳዋለን?

ኢየሱስ ክርስቶስ በአስቸጋሪ ቀናቶቻችን እንዴት እንደረዳን አብዝተን እንናገራለን፣ ይህም የሚሆነው ምናልባትም እያንዳንዱ ሰው በአንድም ሆነ በተለያየ ወቅት አስቸጋሪ ነገሮችን ስለሚጋፈጥ ነው።

ነገር ግን አንዳንድ ቀናት—እድለኞች ከሆንን፣ ሳምንታት ወይም ዓመታት—ነገሮች በእርግጥ በመልካም የሚሄዱበት ጊዜ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ በእነዚያ ጊዜያት አዳኙን እንዘነጋለን። የመፅሐፈ ሞርሞን ህዝቦች ይህንን አድርገዋል። ለጊዜው በእግዚአብሔር በረከቶች በልጽገዋል ነገር ግን በስተመጨረሻ በረሱት ጊዜ በትእቢት ይወድቃሉ።

መልካም ጊዜያት ማለት በድንገት ኢየሱስ ክርስቶስ አያስፈልገንም ማለት አይደለም። የብልጽግና ጊዜያት ጌታን በመርሳት ሳይሆን ከጌታ ጋር ሃሴት የምናደርግበት ፍጹም ጌዜ ነው።

ፈተናዎች ወደ እነርሱ እንድንመለስ በማያስታውሱን ጊኢውቆች፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ እና ከሰማዩ አባታችን ጋር መቆራኘት የምንችለው እንዴት ነው?

ትሁታን ሁኑ

ነገሮች መልካም በሆኑበት ጊዜያት፣ በረከቶቻችሁን እና ስኬቶቻችሁን ማወደስ መልካም ነው። ነገር ግን አሁን ባላችሁበት ስፍራ ላይ መገኛኘታችሁን እውን ያደረገላችሁን አትርሱ። በመጽሀፈ ሞርሞን ስብከቱ ላይ ንጉስ ቢንያም በዚህ መልኩ አስቀምጦታል፦

“እነሆም ሁላችንስ ለማኞች አይደለንምን? ሁላችንም ባሉን ቁሳቁሶች ሁሉ፣ በምግብና በልብስ፣ እንዲሁም በወርቅና፣ በብር፣ እናም ከሁሉም አይነት ባሉን ሀብቶች በአንዱስ ፍጡር፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ጥገኞች አይደለንምን?” (ሞዛያ 4፥19)።

በስኬቶቻችሁ ጊዜያት የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረጉላችሁን ነገሮች በማስታወስ ትሁት መሆን፣ እነርሱን በመልካም ጊዜያቶቻችሁ የማካተት ታላቅ መንገድ ነው።

አመስጋኞች በመሆን ቀጥሉ

አመስጋኝነት ለትእቢት እና ለዝንጉነት ተቃራኒ ከሆኑት አንዱ ነው። እግዚአብሔርን ማመስገን፣ እርሱ እና ልጁ በህይወታችሁ ያደረጉላችሁን ነገሮች ለማስታወስ ይረዷችኋል። ይህ እንደ አስቸጋሪዎቹ ጊዜያት ሆነ በመልካም ቀናት ውጤታማ ነው።

ንቁ በመሆን ቀጥሉ

ከሰይጣን ማጥቂያ መንገዶች አንዱ ‘’ወደ ስጋዊ ደህንነት [እናንተን ማባበል ነው]’’ (2 ኔፊ 28፥21)። በሌላ አባባል፣ በመልካም ጊዜያቶቻችሁ እጅግ አስፈላጊ የሆኑትን በመርሳት ስትረኩ እና ደህንነት ሲሰማችሁ እርሱ ይህንን ይወዳል። ስለዚህ፣ እግዚአብሔርን አትርሱ! የፈታኙን አስከፊ ብልሃቶች ባወቃችሁ ጊዜ እና በመልካም ቀናቶቻችሁ ስትቋቋማቸው፣ ወደ ሰማይ አባት እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይበልጥ መቅረብ ትችላላችሁ።

ወጣት ሴት

መልካሙ እረኛ፣ በሚካኤል ማልም

ክርስቶስን ማእከል በማድረግ ጽኑ

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “የህይወታችን ትኩረት በእግዚአብሔር የደህንነት እቅድ … እና በኢየሱስ ክርስቶስና በወንጌሉ ላይ ሲሆን፣ በህይወታችን ከተከሰተውም ወይም ካልተከሰተውም ሁኔታ ባሻገር ደስታ ሊሰማን ይችላል።” ደስታ ከእርሱና በእርሱ ምክንያት ይመጣል። እርሱ የደስታ ሁሉ ምንጭ ነው።’’

ህይወት በመልካም በሚሄድበት ጊዜ ስለእርሱ እውነት ምን ያህል ታስባላችሁ? ነገሮች ከባድ በሚሆኑበት ጊዜ ብቻ የሚያጽናና ምክር አይደለም። ልዩ ቀናቶቻችሁንም ጨምሮ፣ ይህ ሁል ጊዜ እውነት ነው። ስለዚህ መጥፎም ይምጣ መልካም፣ በክርስቶስ ለማተኮር ማድረግ የምትችሉትን አድርጉ።