ጓደኛ
የአይሁድ ፋሲካ
ሚያዝያ 2026 (እ.አ.አ) ጓደኛ


“የአይሁድ ፋሲካ፣” ጓደኛ፣ ሚያዝያ 2026 (እ.አ.አ)፣ 46–48።

ወርሐዊ የጓደኛ መልእክት፣ ሚያዝያ 20216 (እ.አ.አ)

የአይሁድ ፋሲካ

ሙሴ እና አሮን ከፈርዖን ጋር ሲነጋገሩ የሚያሳይ ስዕል

ሙሴ ወደ ፈርዖን ሄደ እና የእስራኤላውያን ባሮችን ነሻነት እንዲሰጣቸው ጠየቀው። ፈርዖን እምቢ አለ። ጌታ ወደ ግብጽ መቅሰፍት ላከ፣ ፈርዖኑ አሁንም እምቢ አለ።

ሙሴ ከሰዎች ጋር ሲነጋገር የሚያሳይ ስዕል

ጌታ አንድ የመጨረሻ መቅሰፍት እልካለሁ አለ። የእያንዳንዱ ግብጻዊ ቤተሰብ የበኩር ልጅ ይሞታል። እስራኤላውያን የእርሱን መመሪያዎች ከተከተሉ መቅሰፍቱ ከእነርሱ እንደሚያልፍ እና እንደማይጎዳቸው ጌታ ቃል ገባ።

አንድ ሰው፣ ልጆች እየተመለከቱ፣ የበር መቃን እየቀባ የሚያሳይ ስዕል

ጌታ እያንዳንዱ የእስራኤል ቤተሰብ እንከን የለሽ ወንድ ጠቦት መሥዋዕት በማድረግ የጠቦቱን ደም በቤታቸው በር ላይ እንዲቀቡ ነገራቸው።

ፈርዖን ለሞተው ወንድ ልጁ ሲያለቅስ የሚያሳይ ስዕል

መቅሰፍቱ መጣ። የፈርዖን ወንድ ልጅን ጨምሮ፣ ሁሉም የግብጻውያን የበኩር ልጆች ሞቱ። ለጌታ ታዛዥ በመሆናቸው ምክንያት የእስራኤላውያን የበኩር ልጆች ዳኑ።

የተናደደው ፈርዖን ሰራዊት እየላከ የሚያሳይ ስዕል

ፈርዖኑ ሙሴ እና እስራኤላውያን ከግብፅ እንዲወጡ ነገራቸው። ግን ፈርዖኑ ተናድዶ ነበር። እርሱ እና ሰራዊቱ እነርሱን አሳደዱ።

እስራኤላውያን በሰራዊት ሲሳደዱ የሚያሳይ ስዕል

እስራኤላውያን በቀይ ባህር አጠገብ ሰፈሩ። እስራኤላውያን ግብፃውያን ሲመጡ ባዩ ጊዜ ፈርተው ነበር። ሙሴም ጌታ ይጠብቃቸዋል አለ።

ሙሴ ቀይ ባህርን ሲከፍል የሚያሳይ ስዕል

ሙሴም በትሩን ከፍ አደረገ፣ እናም ጌታ ባህሩን ከፈለው። እስራኤላውያን ባሕሩን በደረቅ መሬት ተሻገሩት።

ቀይ ባህር በግብፅ ሰራዊት ላይ ሲመለስ የሚያሳይ ስዕል

እስራኤላውያን ሁሉ በባሕሩ ማዶ በደህና ሲደርሱ፣ ውኃው ተመልሶ የግብጽ ሠራዊትን አሰጠመ። እስራኤላውያን በስተመጨረሻ ነጻ ሆኑ።

የሚቀባ ገፅ

ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ ከሞት ተነስቷል

የአዳኝን ባዶ መቃብርን የሚያሳይ የሚቀባ ገፅ PDF

ስዕል በኦድሪ ደይ። ለቤተክርስቲያኗ ጥቅም ብቻ መባዛት ይቻላል።

በዚህ ፋሲካ እና በአመት በሙሉ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማስታወስ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?