“አዳም እና ሔዋን፣” ጓደኛ፣፣ ጥር 2026 (እ.አ.አ)፣ 46–48።
ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክቶች፣ ጥር 2026 (እ.አ.አ)
አዳም እና ሔዋን
አዳም እና ሔዋን በምድር ከኖሩት የእግዚአብሔር ልጆች መካከል የመጀመሪያዎቹ ነበሩ። በኤደን ገነት ውስጥ ይኖሩ ነበር።
ከአንዱ በስተቀር ከሁሉም የዛፍ ፍሬ እዲበሉ እግዚአብሔር ፈቀደላቸው። መልካምንና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ ከበሉ፣ ከገነት መውጣት አለባቸው እንዲሁም በመጨረሻም ይሞታሉ። ሰይጣን ግን ዋሻቸው። ሰይጣን፣ ፍሬውን ከበሉ መልካምን እና ክፉን ያውቃሉ እንጂ አይሞቱም አለ።
ሔዋን ፍሬውን ለመብላት መረጠች።
ሔዋን ለአዳም ከፍሬው ጥቂቱን ሰጠችው። እርሱም ሊበላው መረጠ።
እግዚአብሔር እና ኢየሱስ ክርስቶስ ጎበኙዋቸው፣ ነገር ግን አዳም እና ሔዋን ፈርተው ነበር እናም ተደበቁ። እግዚአብሔር ከዛፉ ፍሬ በልተው እንደሆነ ጠየቀ።
አዳምና ሔዋን ፍሬውን በልተናል አሉ። አሁን ከኤደን ገነት መውጣት ይኖርባቸዋል። እግዚአብሔር ግን ለእነርሱ እቅድ ነበረው። አሁን መልካምን ከክፉ አውቀው ነበር እንዲሁም ልጆችን መውለድ ቻሉ።
አዳም እና ሔዋን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በሙሉ ለማክበር ቃል ገቡ። ስለ እግዚአብሔር ልጅ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ተማሩ። ቤተሰባቸውን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ እርሱ ሊረዳቸው ስለሚችል ደስተኞች ነበሩ።
ቀለም የሚቀባ ገፅ
ኢየሱስ ምድርን ፈጠረ።
በኦድሪ ዴይ የተሳለ ስዕል
ኢየሱስ ክርስቶስ ከፈጠራቸው ነገሮች ውስጥ ምትወዱት የትኞቹ ናቸው?
© 2026 (እ.አ.አ) by Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ ታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፤ 6/19። Monthly Friend Message, January 2026 (እ.አ.አ) ትርጉም። Language 19919 506