2025
ቅዱሳን ወደ ምዐዕራብ ይሄዳሉ
ታህሳስ 2025 ፟(እ.አ.አ) ጓደኛ


“ቅዱሳን ወደ ምዐዕራብ ይሄዳሉ፣” ጓደኛ፣ ታህሳስ 2025፣ 26-28።

ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ ታህሳስ 2025 (እ.አ.አ)

ቅዱሳን ወደ ምእራብ ይሄዳሉ

ብሪገም ያንግ ህዝቡ ያልተጠናቀቀውን የናቩን ቤተመቅደስ ሲሰሩ እያዩ

ጆሴፍ ስሚዝ ከሞተ በኋላ፣ ብሪገም ያንግ እና ሌሎች ሃዋርያት ቤተክርስቲያኒቱን መርተዋል። ሁኔታው አመቺ ስላልነበር ቅዱሳን ናቩን ለቀው መሄድ እንደነበረባቸው ብሪግሃም ያንግ አውቀዋል። ነገር ግን በመጀመሪያ፣ ጌታ የቤተመቅደሱን ግንባታ እንዲያጠናቅቁ ፈልጓል።

ብሪገም ያንግ ለህዝቡ በቤተመቅደስ አቀባበል ሲያደርጉ

ቤተመቅደሱም ዝግጁ በሆነ ጊዜ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ቅዱሳን ከጌታ ጋር ቃልኪዳንን አደረጉ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተጣምረዋል።

ቅዱሳን ማእበላማ በሆነው በረዶ መካከል ሲያልፉ

አሁን ወደ ምእራብ ጉዟቸውን የሚጀምሩበት ወቅት ነበር። የአየሩ ሁኔታ ቀዝቃዛ ነበር፣ ህዝቡም ታመው እና ተርበው ነበር።

ቤተሰቦች ሌሎች ምግብ እና በቀዝቃዛማው አየር ብርድልብስ እንዲያገኙ እየረዱ

ብሪገም እርዳታ ለማግኘት ጸለዩ። ጌታ እርስ በርስ መረዳዳት እንዳለባቸው እና እርሱም እንደሚባርካቸው እና እንደሚረዳቸው ተናገረ።

አንድ ቤተሰብ ከመቃብር አጠገብ ተንበርክኮ።

አሁንም ጉዞው በጣም ከባድ ነበር። አንዳንድ ሰዎችም ሞቱ። ነገር ግን በቤተመቅደሱ ቃል ኪዳናቸው ምክንያት፣ ቅዱሳን የቤተሰብ አባሎቻችውን ዳግም እንደሚያገኟቸው አውቀዋል።

ብሪግሃም ያንግ በሰረገላ የሶልት ሌክ ሸለቆን አሻግረው ሲመለከቱ

የመጀመሪያዎቹ ቅዱሳን በ1847 (እ.አ.አ) ወደሶልት ሌክ ሸለቆ ደርሰዋል። በዚህ ጌታን ሊያመልኩት እና ስራውንም በሰላም ሊሰሩ ይችላሉ።

የቤተመቅደስ እና የሚስዮናውያን ምስል ከጀርባው የዓለም ካርታ ያለበት

በዓመታት መካከል፣ ብዙ ቅዱሳን ወደዚህ ደርሰዋል እናም ብዙ ቤተመቅደሶችንም ገንብተዋል። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማስተማር በዓለም ዙሪያ ሚስዮናውያንን ተጉዘዋል። በየስፍራው የሰማይ አባት ልጆችን እየባረከች፣ የአዳኙ ቤተክርስቲያን ማደጓን ቀጥላለች።

የሚቀባ ገፅ

እርሱ የአለም ብርሀን፣ ህይወት እና ተስፋ ነው።

ህጻኑ ኢየሱስ በግርግም እና አንዲት የበግ ጠቦት ያለበት የሚቀባ ገጽ PDF

ስዕል በኮሪ ኤግበርት

በገና ወቅት ኢየሱስ ክርስቶስን ለማስታወስ ምን ታደርጋላችሁ?