"ጄን ማኒንግ ወደ ናቩ ተጓዘች፣” ጓደኛ፣ ጥቅምት 2025 (እ.አ.አ)፣ 26–28።
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ ጥቅምት 2025 (እ.አ.አ)
ጄን ማኒንግ ወደ ናቩ ተጓዘች
ጄን ማኒንግ በምትኖርበት ቦታ ውስጥ፣ በቆዳዋ ቀለም ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ያጎሳቁሏት ነበር። አንድ ቀን፣ አንድ ሚሲዮናዊ ሲያስተምር ሰማች። ብዙም ሳይቆይ ተጠመቀች።
የጄን ቤተሰብም ተጠምቀው ነበር። ሁሉም ከቅዱሳን ጋር በናቩ ለመሆን ፈለጉ። በመሆኑም ጉዞአቸውን ጀመሩ።
የጄን ቤተሰብ የጉዞአቸውን ክፍል በጀልባ ለመጓዝ ፈልገው ነበር፣ ግን በቂ የሆነ ገንዘብ አልነበራቸውም። ስለዚህ 800 ማይሎች (1300 ኪሎ ሜትር) በእግር መጓዝ ነበረባቸው።
ጥልቅ ጅረት መሻገር እና አየሩ ብርድ በሆነበት ውጭ መተኛት ነበረባቸው። ነገር ግን ወደ ናቩ ለመድረስ ቁርጠኛ ነበሩ። በጉዞአቸውም ወቅት በመዘመር ራሳቸውን ያነቃቁ ነበር።
የጄን ቤተሰብ ጫማቸው ጨርሶ እስኪያልቅ እና እግራቸውም እስኪጎዳ ድረስ ተጓዙ። እነርሱም እግዚአብሔር እንዲረዳቸው በጸለዩ ጊዜ እግራቸውን ፈውሶላቸዋል።
በጉዞአቸው ወቅት ያገኟቸውን ሰዎች ረድተዋል። በእምነታቸው ምክንያት የታመመን ልጅ በመፈወስ ረድተዋል።
በመጨረሻም፣ ጄን እና ቤተሰቧ ወደ ናቩ ደረሱ! ጆሴፍም ያለፉበትን ሁሉ ሲሰማ፣ ለጄን እንዲህ አላት፣ ‘’እግዚአብሔር ይባርክሽ። አሁን በጓደኞች መካከል ነሽ።’’
የሚቀባ ገፅ
ኢየሱስ ሁሉንም እንድወድ ይፈልጋል
ስዕል በኮሪ ኢግበርት
ሌሎችን እንደምትወዱ የምታሳዩት እንዴት ነው?
© 2025 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, October 2025 ትርጉም። Amharic. 19630 506