“ናቩን መገንባት፣” ጓደኛ፣ መስከረም 2025 (እ.አ.አ)፣ 26-28።
ወርሃዊ የጓደኛ መልዕክት፣ መስከረም 2025 (እ.አ.አ)
ናቩን መገንባት
ጌታ ቅዱሳን በአዲስ ቦታ እንዲሰበሰቡ ነገራቸው። ይህም መሬቱ እርጥበታማ እና ጭቃማ በነበረበት በትልቅ ወንዝ አጠገብ ነበር። ይህ ቦታ ከተማን ለመገንባት ጥሩ ቦታ አይመስልም ነበር። ነገር ግን ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በጌታ እርዳታ ውብ ሊያደርጉት እንደሚችሉ ያውቅ ነበር።
ቅዱሳኑ ይህን ጥሩ የመኖሪያ ቦታ ለማድረግ ጠንክረው መሥራት ጀመሩ። ነቢዩ ጆሴፍ ከተማዋን ናቩ ብሎ ጠራት፣ ትርጉሙም “ውብ ቦታ” ማለት ነው።
ጌታ፣ ቅዱሳኑ በአንድነት በናቩ ውስጥ ቤተመቅደስን እንዲገነቡ ፈልጎ ነበር። ህዝቡም በፍጥነት መሥራት ጀመሩ።
ጌታ ለህዝቦቹ ሊሰጥ የነበረው ታላቅ በረከት ነበረው። በቤተመቅደስ ውስጥ፣ ከጌታ ጋር ቃል ኪዳኖችን፣ ወይም ልዩ ቃል፣ ይገባሉ። እንዲሁም የሰማይ አባት ለሁሉም ልጆቹ ስላለው የደስታ እቅድ ይማራሉ።
ቤተመቅደሱን ለመገንባት ቅዱሳን ጠንክረው ሰሩ። ብዙ ጊዜ ወሰደባቸው፣ ነገር ግን እያንዳንዳቸው በቤተመቅደሱ ውስጥ ጌታ ስለሚሰጣቸው ልዩ ቃል ኪዳኖች ለሚማሩበት ቀን ጓጉተው ነበር።
የሚቀባ ገፅ
ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው።
ምስል በኮሪ ኢግበርት
ቤተመቅደስን ስትመለከቱ ምን ተሰማችሁ?
© 2025 by Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ ታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፤ 6/19። Monthly Friend Message, September 2025 ትርጉም። Amharic. 19640 506