“ሊበርቲ እስር ቤት፣” ጓደኛ ነሐሴ 2025 (እ.አ.አ)፣ 26–28።
ወርሀዊ የጓደኛ መልዕክት፣ ነሐሴ 2025 (እ.አ.አ)
ሊበርቲ እስር ቤት
በሚዙሪ ይኖሩ የነበሩ ብዙ ሰዎች ቅዱሳኑን አይወዷቸውም ነበር። የአገረ ገዢውም እነርሱን ለማስወጣት ወታደሮችን ላከ።
ወታደሮቹ ጆሴፍ ስሚዝን እና ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎችን አሰሩ። በአንድ ሌሊት፣ጠባቂዎቹ በቅዱሳን ላይ ስላደረጓቸው መጥፎ ነገሮች እያወሩ ሲስቁ ጆሴፍ እና ሌሎች እስረኞች ሰሙ።
ጆሰፍ ቆመ እናም በቁጣ፣ ‘’ፀጥታ!’’ በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ። እርሱ ይናገር የነበረው በእግዚአብሔር ሃይል ነበር። ጠባቂዎቹ ይቅርታ በማለት ንግግራቸውን አቆሙ።
በኋላም፣ ጆሰፍ እና ጓደኞቹ ሊበርቲ በሚባል ከተማ ወደ ነበረ አንድ እስር ቤት ተወሰዱ። እስር ቤቱ ቀዝቃዛ፣ ትንሽ እና ጨለማ ነበር። የነበራቸውም የሚተኙበት የቆሸሸ የሳር ፍራሽ ብቻ ነበር። የተሰጣቸው ምግብ እንዲታመሙ አደረጋቸው።
ጆሴፍ ስለቅዱሳኑ ተጨነቀ። ነገር ግን እነርሱን ለመርዳት ሊያደርግ የሚችለው ነገር አልነበረም።
ጆሴፍ አብዝቶ ፀለየ። እግዚአብሔር እርሱን እና የቤተክርስቲያኗን አባላት ረስቶ እንደሆነ ጠየቀ።
እግዚአብሔር ለጆሴፍ ጸሎት ምላሽ ሰጠ። እንዲህም አለ፣ ‘’ልጄ ሆይ፣ ለነፍስህ ሰላም ይሁን ።’’ እግዚአብሔር፣ ፈተናዎቹ ለዘለዓለም የሚቆዩ እንዳልሆኑ እና ለመልካም እንደሚሆኑለት ለጆሴፍ ነገረው። ‘’ለዓለም እና ለዘለዓለም’’ ከጆሴፍ ጋር እንደሚሆን ቃል ገባለት(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121:7፣ 46)።
የሚቀባ ገፅ
ለሌሎች እንደ ብርሀን ለመሆን እችላለሁ።
ምስል በኮሪ ኢግበርት
ለሌሎች መልካም አርአያ የሆናችሁት እንዴት ነው?
© 2025 by Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ ታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፤ 6/19። Monthly Friend Message, August 2025 (እ.አ.አ) ትርጉም። Amharic. 19642 506