2025
ሐዋርያት በታላቋ ብሪታንያ ሚስዮን አገለገሉ
ግንቦት 2025 (እ.አ.አ)


ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ ሐምሌ 2025 (እ.አ.አ)

ሐዋርያት በታላቋ ብሪታንያ ሚስዮን አገለገሉ

ጆሴፍ ስሚዝ ሐዋርያት በታላቋ ብሪታንያ ወንጌልን ሲሰብኩ በምናቡ አሰበ

ጌታ አንዳንድ ሐዋርያትን ለሚስዮን ወደ ታላቋ ብሪታንያ እንዲልክ ለጆሴፍ ስሚዝ ነገረው። ቤተሰቦቻቸውን ትተው መሄድ ለሐዋርያትም ከባድ ነበር፣ ነገር ግን ጌታ ሊባርካቸው ቃል ገብቶላቸዋል።

የኪምቦል ቤተሰብ በህመም አልጋ ላይ

ሒበር ሲ. ኪምባል እና ሚስቱ ቪላቴ ታዳጊ ቤተሰብ ነበራቸው። ከእነርሱም ብዙዎቹ ታመው ነበር።

ብሪገም ያንግም ቤተሰቦቹን ሲሰናበት

ብሪገም ያንግም እንዲሁ ታምሞ ነበር፣ እና ቤተሰቡም ድሃ ነበር። ነገር ግን የብሪገም ሚስት፣ ሜሪ አን፣ “ሂድ እና በሚስዮን አገልግል፣ ጌታም ይባርክሃል” አለችው።

ሒበር እና ብሪግሃም በሠረገላ ላይ ሆነው ሲጓዙ

ሒበር እና ብሪግሃም ተሽሏቸው ነበር፣ ሆኖም በጣም አቅም አንሷቸው ነበር። ወንጌልን ለመስበክ ፈልገዋል፣ በመሆኑም ቤተሰቦቻቸውን ተሰናበቱ እናም ጉዞአቸውንም ለመጀመር በአንድ ሰረገላ ኋላ ወጡ።

ብሪግሃም እና ሒበር በታላቋ ብሪታንያ ለነበሩ ሕዝቦች ወንጌልን እየሰበኩ።

ከውቅያኖሱ ባሻገር ረጅም ጉዞ ካደረጉ በኋላ፣ ሒበር እና ብሪግሃም ወደ ታላቋ ብሪታንያ ደረሱ። ከሌሎች ሐዋርያት ጋር፣ አያሌ ሰዎችን ወንጌል አስተማሩ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአዳኙ ቤተክርስቲያን ተጠምቀዋል። ከእነርሱም አብዛኞቹ በዩናይትድ ስቴትስ የነበሩ ቅዱሳንን ለመቀላቀል ከውቂያኖስ ባሻገር ተጉዘዋል።

የሒበር እና የብሪግሃም ቤተሰቦች በዳርቻው ላይ ሰላምታ ሲያቀርቡላቸው

እነርሱ በሚስዮናዊ አገልግሎት ላይ ሳሉ ጌታ የሒበርን እና የብሪግሃምን ቤተሰብ እንደሚንከባከባቸው የገባውን ቃል ጠበቀ።

የሚቀባ ገፅ

እግዚአብሔር በምድር ላይ ያለውን ፍጥረት ሁሉ ፈጠረ።

ድመትን፣ ቢራቢሮን፣ እና አበባን የማቅለም አክቲቪቲ PDF

ምስል በኮሪ ኢግበርት

የምትወዱት ፍጥረት ምንድነው?