ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ ሰኔ 2025 (እ.አ.አ)
የከርትላንድ ቤተመቅደስን መገንባት
ጌታ በከርትላንድ፣ ኦሃዮ፣ ዩ.ኤስ.ኤ ቤተመቅደስ የሚሰራበት ጊዜው እንደሆነ ለጆሴፍ ስሚዝ ነገረው። ይህም ጌታ ህዝቡን የሚጎበኝበት እና ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን የሚገባበት ልዩ ስፍራ ይሆናል።
ቅዱሳን ቤተመቅደስን መስራት ጀመሩ። ብዙ ወጪ ጠይቋል እና ብዙም ስራም አስፈልጎታል። ነገር ግን የጌታን በረከት በመቀበላቸው ተደስተው ነበር።
ቅዱሳን ቤተመቅደስ እየገነቡ እያሉ፣ የገንዘብ እጥረት ገጠማቸው። እነርሱም እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ጸለዩ።
ኬሮሊን ቲፔትስ የተባለች ሴት እና ቤተሰቧ ብዙ ገንዘብ ቆጥበው ነበር። የቤተመቅደሱን ግንባታ ለመርዳት ቤተክርስቲያኗ ገንዘቡን እንድትበደር ፈቀዱ።
ቅዱሳን በትጋት ሰሩ። አንዳንዶቹ ድንጋይ የሞላባቸውን ጋሪዎች ይነዱ ነበር። ሌሎች ደግሞ ለሰራተኞች አልባሳትን እና ምግብ ይሰሩ ነበር።
ልጆችም የቤተመቅደስ ግድግዳዎችን እንዲያንጸባርቁ እና በጸሀይ ብርሃን እንዲያበሩ ለማድረግ ስብርባሪ ብርጭቆዎችን ሰበሰቡ።
ወዲያውኑም ቤተመቅደሱ ተገባደደ! ጌታ ቃል የገባላቸውን በረከቶች ለመቀበል ቅዱሳን ወደ ጌታ ቤት ለመሄድ ተደስተው ነበር።
የሚቀለም ገፅ
ጌታ ማን እንደሆንኩኝ ያውቃል እንዲሁም ይወደኛል።
ስዕል በኮሪ ኢግበርት
በሞላላው ቅርጽ ውስጥ የራሳችሁን ፊት ሳሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚወዳችሁ የምታውቁት እንዴት ነው?
© 2025 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, June 2025 ትርጉም። Amharic. 19643 506