“ሉሲ እውነትን አገኘች፣” ጓደኛ፣ ሚያዚያ 2025፣ 26–28
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ ሚያዝያ 2025 (እ.አ.አ)
ሉሲ እውነትን አገኘች
አንድ ቀን፣ የ15 ዓመቷ ሉሲ ሞርሊ ጎረቤቷ አቢግኤል ዳኒልስን ልብስ ስትሠፋ እየረዳቻት ነበር። በሥራ ላይ እያሉ ሦስት ሚስዮናውያን በሩን አንኳኩ። ኢየሱስ ክርስቶስ መልዕክት እንዲያካፍሉ እንደላካቸው ተናገሩ።
ጆሴፍ ስሚዝ ነቢይ ይሆን ዘንድ ኢየሱስ እንደጠራው ሠዎቹ ለአቢግኤል እና ለሉሲ ነገሯቸው። በተጨማሪም፣ ስለመፅሐፈ ሞርሞን ነገሯቸው።
አቢግኤል በመናደዷ ሉሲ ተገረመች። ሚስዮናውያን እንዲወጡ አደረገች።
ሉሲ እነዚህ ሚስዮናውያን የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንደሆኑ አወቀች። መንገድ ላይ ያሉትን ቤተሰቦቿን እንዲጎበኙ ነገረቻቸው።
ሚስዮናውያኑ ወደ ሞርሊ ቤት ሄዱ። የሉሲ ወላጆች ሚስዮናውያን እነሱን እና ጓደኞቻቸውን እንዲያስተምሩ ጋበዟቸው።
በዚያ ምሽት 17 ሰዎች ተጠመቁ። በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ 50 ተጨማሪ ሰዎች ሚስዮናውያንን ሰምተው ተጠመቁ። የሉሲ ጎረቤት አቢግያ እንኳን ሃሳቧን ቀየረች። እርሷ እና ባለቤቷ ከሉሲ እና የቤተሰቧ አባት ጋር በመጠመቅ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል መረጡ።
የሚቀባ ገፅ
በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት፣ በትንሳኤ እነሳለሁ
ስዕል በኮሪ ኢግበርት
በፋሲካ ጊዜ ኢየሱስን እንዴት ነው የምታስታውሱት?
© 2025 (እ.አ.አ) በ Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Translation of Monthly Friend Message, April 2025.ትርጉም Amharic. 19631 506