“ክህነት ተመልሷል፣” ጓደኛ፣ መጋቢት 2025፣ (እ.እ.አ) 26–28
ወርኃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ መጋቢት 2025 (እ.አ.አ)
ክህነት ተመልሷል
ይህንን ታሪክ በ ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥66-73 እና ትምህርት እና ቃልኪዳን 27፡12ውስጥ ማንበብ ትችላላችሁ።
ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሳህኖቹን ከተቀበለ በኋላ፣ መተርጎም ጀመረ። ኦሊቨር ካውደሪ የተናገረውን ጻፈ። እየሰሩ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉም ሰው እንዲጠመቅ እንደሚፈልግ ተማሩ።
ጆሴፍ እና ኦሊቨር ሰዎችን ለማጥመቅ የእግዚአብሔር ኃይል ያለው ማን እንደሆነ አሰቡ። እግዚአብሄርን ለመለመን ጫካ ውስጥ ገቡ።
ሲጸልዩ አንድ መልአክ ብቅ አለ። ከጥንት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስን ያጠመቀው መጥምቁ ዮሐንስ እንደሆነ ተናገረ። ሌሎችን እንዲያጠምቁ ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር የአሮናዊ ክህነት ሰጣቸው። ክህነት የእግዚአብሔር ኃይል ነው። የእግዚአብሔርን ልጆች ለመባረክ ያገለግላል።
መጥምቁ ዮሐንስ ለጆሴፍና ለኦሊቨር እንዲጠመቁ ነገራቸው። ከዚያም ወደ አንድ ወንዝ ሄደው አንዱ ሌላውን አጠመቀ። ከውኃውም በወጡ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ። በጣም ተደሰቱ!
ከጊዜ በኋላ ሌሎች መላዕክት መጡ። ሦስቱ የኢየሱስ ሐዋርያት—ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ—ለጆሴፍ እና ለኦሊቨር የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ሰጡ። አሁን ጆሴፍና ኦሊቨር የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ለሌሎች መስጠት ይችላሉ።
የሚቀለም ገፅ
ኢየሱስ “ከልብ የሆነ ዝማሬን” ይወዳል።
ስዕል በኮሪ ኢግበርት
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስትዘምሩ ምን ይሰማችዋል?
© 2025 (እ.አ.አ) በ Intellectual Reserve, Inc. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የ ወርሃዊ የጓደኛ መልዕክት, መጋቢት2025(እ.አ.አ.) ትርጉም። Amharic. 19636 506