2025
ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሰሌዳዎችን ተቀብሏል
የካቲት 2025 (እ.አ.አ)


“ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሰሌዳዎችን ተቀበለ፣” ጓደኛ፣ የካቲት 2025 (እ.አ.አ) 26-28

“መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ምስክር መሆን እችላለሁ።ጓደኛ የካቲት 2025 48

ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክት፣ የካቲት 2025 (እ.አ.አ)

ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሰሊዳዎችን ተቀብሏል

ይህንን ታሪክ በ ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥28–60 ውስጥ ማንበብ ትችላላችሁ።

ጆሴፍ ስሚዝ በመስኮት ወደ ውጪ ሲመለከት።

ከመጀመሪያ ራእይ ከሶስት ዓመት በኋላ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ስለሰራቸው አንዳንድ ስህተቶች በራሱ አዝኖ አዘነ። ከዚያም ወደ ሰማይ አባት ስለ ጉዳዩ ጸለየ።

ጆሴፍ ስሚዝ ለጸሎት ተንበርክኮ

ጆሴፍ እየጸለየ ሳለ ብርሃን ክፍሉን ሞላው። አንድ መልአክ ከአጠገብ በአየር ላይ ቆሞ አየ። መልአኩ ስሙ ሞሮኒ ይባል ነበር።

መልአኩ ሞሮኒ ጆሴፍ ስሚዝን በክፍሉ ውስጥ ጎበኘው።

ሞሮኒ ከወርቅ ገጾች ወይም ሰሌዳዎች የተሠራ መጽሐፍ መኖሩን ተናገረ። የተቀበረውም በጆሴፍ ቤት አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ኮረብታ ላይ ነበር። መጽሐፉ ከረጅም ጊዜ በፊት በአሜሪካ አገር ስለኖሩ ሰዎች የሚናገር ነበር። ጆሴፍ መጽሐፉን እንዲተረጉም እግዚአብሔር እንደሚረዳው ሞሮኒ ተናገረ።

ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሰሌዳዎችሁን ለመመልከት ወደ ጉድጓዱ ሲመለከት።

ጆሴፍም ወደ ኮረብታው ሄዶ የወርቅ ሰሌዳዎቹን ከከባድ ዓለት ስር አገኘ። ሞሮኒ መጥቶ ለጆሴፍ ሰሌዳዎቹን ለመውሰድ ዝግጁ አለመሆኑን ነገረው።

መልዓኩ ሞሮኒ ለጆሴፍ ስሚዝ ሲያናግረው።

ጆሴፍ ስሚዝ እድሜው ከፍ ባለ ጊዜ፣ ሞሮኒ በኮራብታ አገኘው እናም ሰሌዳዎቹን ሰጠው። ሞሮኒም ጆሴፍን በጥንቃቄ እዲጠብቃቸው ነገርው።

ጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰቡን እያነጋገረ

ጆሴፍ ሰሌዳዎቹን ወደ እንግሊዘኛ መተርጎም ጀመረ። እግዚአብሄር እሱን ለመርዳት ያዘጋጃቸውን ልዩ መሣሪያዎች ተጠቀመ። መጽሃፉም መፅሐፈ ሞርሞን ተብሎ በ1830 ታተመ (እ.አ.አ) ነው። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስና ስለ ወንጌሉ ያስተምራል።

የሚቀለም ገፅ

መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ምስክር መሆን እችላለሁ።

የማቅለሚያ ገጽ ሴት ሕጻን ልጅ መጽሃፍ ሞርሞን ታቅፋ።

ስዕል በኮሪ ኢግበርት

ሌሎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማወቅ እንዲችሉ እንዴት ነው መርዳት የምትሉት?