“የመጀመሪያው ራዕይ፣” ጓደኛ፣ ጥር 2025 (እ.አ.አ) 26–28።
ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክቶች፣ ጥር 2025 (እ.አ.አ)
የመጀመሪያው ራዕይ
ይህንን ታሪክ በ ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥1–20 ውስጥ ማንበብ ትችላላችሁ።
ጆሴፍ ስሚዝ ወጣት እያለ፣ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተለያዩ ነገሮችን ያስተምሩ ነበር። ጆሴፍ የትኛውን ቤተ ክርስቲያን እንደሚቀላቀል አያውቅም ነበር።
አንድ ቀን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያዕቆብ 1፥5ን አነበበ። ጥበብ ከፈለግን እግዚአብሔርን ልንጠይቀው እንችላለን ይላል። ጆሴፍ ይህን ለማድረግ ወሰነ።
በሚያምር የፀደይ ቀን፣ ጆሴፍ ወደ የሰማይ አባት ለመጸለይ ወደ ጫካው ገባ።
ጆሴፍ ተንበርክኮ መጸለይ ጀመረ። ከዚያ በኋላ ግን በዙሪያው ጨለማ ሲከበው ተሰማው። ጆሴፍ ፈርቶ ነበር። እሱም እግዚአብሔር እንዲረዳው ጠየቀ።
በድንገት ጆሴፍ ብርሃን ከሰማይ ሲወርድ አየ። የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን በአየር ላይ ቆመው አየ። የሰማይ አባት የጆሴፍን ስም ጠራ። ከዚያም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየጠቆመ፡- “ይህ የምወደው ልጄ ነው። አድምጠው!”
ኢየሱስ ወደ የትኛውም ቤተ ክርስቲያን መቀላቀል እንደሌለበት ለጆሴፍ ነገረው።
ጆሴፍ በምድር ላይ የወንጌልን ሙላት ለመመለስ ይረዳል።
ጆሴፍ ከዚህ በኋላ ግራ አልተጋባም። በደስታ ተሞላ። እግዚአብሔር እንደሚወደው አወቀ። አንዳንድ ሰዎች የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን አይቷል ብለው አላመኑም ነበር፣ ነገር ግን እውነት መሆኑን ያውቅ ነበር።
የሚቀለም ገፅ
የሰማይ አባት ጸሎቴን ይሰማል እንዲሁም መልስ ይሰጣል
ስዕል በኮሪ ኢግበርት
የሰማይ አባት ለጆሴፍ ስሚዝ ጸሎት መለሰ። እርሱ ለእናንተም መልስ ይሰጣል!
© 2025 (እ.አ.አ) በ Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, January 2025ትርጉም። Amharic. 19632 506