“ነብዩ ጴጥሮስ፣” ጓደኛ፣ ሐምሌ 2023 (እ.አ.አ)፣ 46-47።
ወርሃዊ ጓደኛ መልእክቶች፣ ሐምሌ 2023 (እ.አ.አ)
ነብዩ ጴጥሮስ
ሥዕል በኤፕርል ስቶት
ኢየሱስ ክርስቶስ አርጎ ወደ ሰማይ ከሄደ በኋላ፣ ጴጥሮስ ነብይ ሆነ።
ጴጥሮስ ሰዎችን ስለጥምቀት እና ስለመንፈስ ቅዱስ አስተማረ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለመጠመቅ ወሰኑ!
አንድ ቀን ጴጥሮስ ከቤተ-መቅደስ ውጪ አንድ ሰው አየ። ሰውየው መራመድ አይችልም ነበር። ጴጥሮስም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ ተነስተህ ሂድ አለ።
ሰውየው ባለው እምነት የተነሳ ተፈወሰ። ጴጥሮስ በቤተ-መቅደስ ለነበሩትን ሰዎች ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተማረ።
የሚቀባ ገፅ
ስለኢየሱስ ለሌሎች መንገር እችላለሁ
ሥዕል በኤፕርል ስቶት
© 2023 (እ.አ.አ) በ Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, July 2023. ትርጉም። Language. 19045 506