2023 (እ.አ.አ)
ኢየሱስ አንዲትን ሴት ፈወሰ
የካቲት 2023 (እ.አ.አ)


“ኢየሱስ አንዲትን ሴት ፈወሰ” ወርሀዊ የ ጓደኛ መልእክቶች፣ የካቲት 2023 (እ.አ.አ)

“ኢየሱስ አንዲትን ሴት ፈወሰ”

ወርሃዊ የ ጓደኛ መልእክቶች፣ የካቲት 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ አንዲትን ሴት ፈወሰ

ኢየሱስ በመንገድ ላይ እየተጓዘ

ሥዕል በኤፕሪል ስቶት

አንድ ቀን ኢየሱስ በተጨናነቀ መንገድ ላይ እየሄደ ነበር። በግርግሩ ውስጥ ለ12 ዓመታት በሽተኛ የነበረች አንዲት ሴት ነበረች።

አንዲት ሴት የኢየሱስን ልብስ እየነካች

ሴቲቱ ኢየሱስ ሊፈውሳት እንደሚችል እምነት ነበራት። እጇን ዘርግታ ልብሱን ነካችው። እሷም ወድያው ተፈወሰች!

ኢየሱስ ክርስቶስ

“ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው?” ሲል ጠየቀ ኢየሱስ። ሴቲቱ ፈርታ ነበር። በኢየሱስ ፊት ተንበረከችና የሆነውን ነገረችው።

ኢየሱስ ከአንዲት ሴት ጋር ሲነጋገር

ኢየሱስ አፍቃሪ ነበር። “አይዞሽ“ አላት። በእምነቷ ምክንያት እንደተፈወሰች ነገራት።

ልጆች በጀልባ ውስጥ

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት ሊኖረኝ ይችላል። ፍቅሩ ሊረዳኝ እና ሰላም ሊያመጣልኝ ይችላል።

የሚቀባ ገፅ

በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት አለኝ።

እናት እና ወንድ ልጅ እየጸለዩ

ለማውረድ ስዕሉ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

ሥዕል በኤፕሪል ስቶት

እምነታችሁን የምታሳዩት እንዴት ነው?