“ቤተክርስቲያኗ በአለም ዙሪያ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)።
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ ታህሳስ 2021 (እ.አ.አ)
ቤተክርስቲያኗ በአለም ዙሪያ
ሥዕል በኤፕርል ስቶት
ጌታ ለቤተክርስቲያኗ አባላት ወደ ሩቅ ቦታ እንዲሄዱ ነገራቸው። አንዳንዶቹ የተሸፈኑ ሰረገላዎችን ነዱ። አንዳንድ የእጅ ጋሪዎችን ጎትተዋል።
ለመኖር ወደ አዲስ ቦታ ሄዱ። ቤቶችን እና ከተማዎችን ገነቡ። አዳዲስ ቤተመቅደሶችን ገነቡ።
ሚስዮናውያን ወደ ብዙ አገሮች ሄዱ። ሌሎችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተማሩ። ብዙ ሰዎች ተጠምቀው ነበር። ቤተክርስቲያኗ አደገች።
ዛሬ፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት በመላው አለም ውስጥ ይኖራሉ። በብዙ አገሮች ውስጥም ቤተመቅደሶች አሉ።
የትም ብንኖርም፣ ኢየሱስ ይወደናል። እንደሚወደኝ አውቃለሁ!
የሚቀባ ገፅ
ኢየሱስ ሁላችንንም ይወዳል
ለማውረድ ስዕሉ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
ሥዕል በኤፕርል ስቶት
የኢየሱስ ፍቅር እንዴት ይሰማችኋል?
© 2021 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. Printed in USA. እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, December 2021 ትርጉም። Amharic. 17476 506