Guatemala: Recess

የተመጣጠነ ምግብ አመጋገብን በማሻሻል የእግዚአብሔርን ልጆችን መንከባከብ

እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል፣ በአለም ዙሪያ ያሉትን ሁሉንም የእግዚአብሔር ልጆች ለመንከባከብ ቃል ገብተናል። የዚህ ጥረት አንዱ ዓላማ ልጆቻችን ያላቸውን አቅም በተሟላ ሁኔታ እንዲጠቀሙበት ማገልገልና መንከባከብ ነው።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዚዳንት ከሚል ኤን. ጆንሰን

ልጆችን የተመጣጠነ ምግብ ስለመመገብ መግቢያ

የተመጣጠነ የምግብ አመመገብ አስፈላጊነት

በአለም ላይ ብዙ ልጆች በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ይሰቃያሉ። በተለይ ከፅንስ ጊዜ ጀምሮ ከ2-3 አመት እድሜ ድረስ፣ ጤናማ አመጋገብ ለትክክለኛው የአንጎል፣ የአካል እና የበሽታ መከላከል ስርዓት እድገት አስፈላጊ ነው። አንድ ልጅ በዚህ ጊዜ ውስጥ ተገቢውን የተመጣጠነ ምግብ ካላገኘ፣ የአንድ ልጅ አንጎል እና አካል ማደግ ያለበትን ያህል አያድግም።

ለልጆች የሚሰጥ አጠቃላይ እንክብካቤ

ቤተክርስቲያኗ የተመጣጠነ ምግብ አመጋገብ፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ በድገፋ የአካባቢ የህክምና አገልግሎት እና ሌሎች የልጆች እድገት አቅምን ለማሟላት የሚረዱ ነገሮችን በማቅረብ፣ ብዙ ልጆች የተመጣጠነ ምግብ አጠቃላይ እንክብካቤ እርዳታ እንዲያገኙ የመርዳት ጥረቶች ላይ ትኩረት አድርጋለች።

ለወላጆች እና ለመሪዎች መገልገያዎች

ቤተክርስቲያኗ ለወላጆች እና መሪዎች ልጆችን እና ቤተሰቦችን ለመደገፍ በሚፈልጉበት ጊዜ ሀሳቦችን እና መረጃዎችን በማቅረብ ብዙ መመሪያዎችን አዘጋጅታለች። መመሪያዎቹን በአርዕስታቸው መሰረት ማውረድ ወይም ሁሉንም ከዚህ በታች በሚገኙት መገናኛዎች መሰረት ማውረድ ትችልላችሁ።

ለቤተሰቦች የሚሆኑ መመሪያዎች

ለመሪዎች የሚሆኑ መመሪያዎች

የቤተሰብ መመሪያ መፅሐፍ (ሁሉንም የቤተሰብ መመሪያ መፅሐፎችን ይዟል)
የቀለም ትግበራ መፅሐፍ
የክፍል መሪ በፍጥነት ለመጀመር የሚረዳ መመሪያ
የመሪ መመሪያ መፅሐፍ (ሁሉንም የመሪ መመሪያ መፅሐፎችን ይዟል)

Malnutrition Resources

Wellness and Nutrition

Prácticas de higiene y seguridad

ቤተክርስቲያኗ ለመርዳት ምን እንደምታደርግ ተመልከቱ

ተሳተፉ።

በአለም ዙሪያ ባሉ ማህበረሰቦች ውስጥ ልጆች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያጋጥማቸዋል። ስለ ልጅ የተመጣጠነ ምግብ አመጋገብ፣ ቤተሰባችን እንዴት እንደሚጎዳ እና እናንተ እንዴት መርዳት እንደምትችሉ የበለጠ ለማወቅ ከዚህ በታች ያሉትን ምንጮች ተጠቀሙ።

እንዴት ልሳተፍ እችላለሁ?

በጸሎት እና በመንፈስ ቅዱስ ምሪት አማካኝነት በማህበረሰባችሁ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን ለመርዳት መንገዶችን ልታገኙ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ የጾም በኩራትን በለጋስነት መስጠት፣ በአካባቢያችሁ በእርዳታ የተገኙ ምግቦች ማከማቻ ውስጥ በፈቃደኝነት መስራት ወይም ለጎረቤታችሁ የተመጣጠነ ምግብን ማዘጋጀት ትችላላችሁ። በአካባቢያችሁ የሚገኝ ከሆነ፣ JustServe.orgን በመጎብኘት እና የልጆች አመጋገብ ወይም ከረሃብ ጋር የተያያዙ ፕሮጀክቶችን በመፈለግ በዚህ ጥረት ውስጥ መሳተፍ ትችላላችሁ።